Patriarchs and Blessed Archbishops of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church! P2

Part 2 ….

የቀደመውን ማየት ከፈለጉ click this link

3. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት


ሦስተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ አቡነ ተክለሃይማኖት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በታሠሩ በ5 ወራት ከ2 ቀናቸው ሐምሌ 11ቀን ኤጲስ ቆጶስ ፤ ከአንድ ወር ከ12 ቀናት በኋላ ነሐሴ 23 ቀን ዕሁድ 1968 ዓ/ም ደግሞ 3ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ሆነው ተሾሙ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን አገልግሎት በመቀጠል በዘመናቸው የአብነት ትምህርት ቤቶችን ፤ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትንና የሰንበት ትምህርት ቤት እንቅስቃሴን በበለጠ አስፋፍተዋል ፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ለ1 ወር ከ12 ቀናት በኤጲስ ቆጶስነት ፤ ለ11 ዓመታት ከ9 ወራትና ከ10 ቀናት በፓትርያርክነት ካገለገሉ በኋላ ግንቦት 28 ቀን 1980 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ ፡፡

4. አቡነ ጳውሎስ (1928 ዓ.ም-2004 ዓ.ም).


በዘመነ ዮሐንስ በዓድዋ ከተማ በመደራ አባ ገሪማ ገዳም አካባቢ ከካህን ቤተሰብ፣ ከአባታቸው ከአፈ መምህር ገብረ ዮሐንስ ወልደ ሥላሴና ከእናታቸው ከወ/ሮ አራደች ተድላ ሲወለዱም የተሰጣቸው ስም ገ/መድህን ነበር፡፡ አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳሳ ዘአክሱም፣ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንት ቤተክርስቲያኒቱን ለ20 ዓመት ካስተዳደሩ በኋላ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከንጋቱ 11:00 ሰአት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለዩ።


“የኢትዮጵያ ጳጳሳት ሰም ዝርዝራቸው”
#ታደለ ጥበቡ
Share, በማድረግ ማሳወቅ መልካመነት ነው!
——————++++++++———————-
በአብርሃና በአጽብሃ ዘመን የነበሩ
1-ግሪካዊው ቅዱስ ፍሬምናጦስ (አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን)
-እነህ አባት የመጀመሪያው ጳጳስ ናቸው።ከአክሱም ወደ ግብጽ በ325 አ.ም ሄደው በ20ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ አቡነ አትናቴዎስ “ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ” ተብለው በቅባትና በአንብሮተ እድ ሹሞ ልኮታል።
(ታሪካቸውን ለማንበብ ለጠየቃችሁኝ
-Historieb Ecclesiastic,p.L.xxi.478-80
-A London,the lesser Ebstefn churches,London,1913 p.295
-storia D’Ethiopia,C.Rossini,p 149-151 ተመልከቱ)
-ፍሬምናጦስ ጳጳስ የሆነው በ341 አ.ም ሲሆን በ350 አ.ም ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነ አንዳዶች በ315 ይሉታል ሩፊኖስ ግን በ350 ነው የሚለው።
(RufInus loc.cit l.ix
2-አቡነ ሚናስ ካልዕ(ሰላማ)ናቸው።አንዳዶች አባ ሙሴ ይሏቸዋል።
-ዘመኑ በንጉሥ እለዓሜዳ ዘመነ መንግሥት ነው(471-479) በዚህን ጊዜ ዘጠኙ ቅዱሳን (አረጋዊ፣ጰንጠሊዮን፣ገሪማ፣ሊቃኖስ፣ይምዓታ፣ፅህማ፣ጉባ፣አፍፄ እና አሌፍ)በ480 አ.ም ከሶርያና ከታናሿ እስያ ይታመናል።
3-አባ ጴጥሮስ 1ኛ 4-አባ ማቴዎስ 1ኛ
5-አባ ማርቆስ 1ኛ 6-አባ ዮሐንስ 1ኛ
7-አባ ገብርኤል 1ኛ 8-አባ ዮሐንስ 2ኛ
9-አባ ገብርኤል 2ኛ 10-አባ ሚናስ 2ኛ
11-አባ ሚካኤል 1ኛ 12-አባ ይስሐቅ
13-አባ ስምዖን 1ኛ 14-አባ ጴጥሮስ 2ኛ
15-አባ ሚካኤል 2ኛ 16-አባ ገብርኤል 3ኛ
17-አባ ዮሐንስ 3ኛ 18-አባ ማቴዎስ 2ኛ
@ የዛጎዌ ስርዎ ክርስቶስ ወይንም ገብረማርያም በመራ ተክለሃይማኖት (912-925 አ.ም ) ከተመሰረተ በኋላ በሰባተኛው ንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስ (1077-1157 አ.ም)ጀምሮ የነበሩት:-
19-አባ ሚካኤል 3ኛ 20-አባ ስምዖን 2ኛ
21-አባ ዮሐንስ 4ኛ 22-አባ ማርቆስ 2ኛ
23-አባ አብርሃም ናቸው።
-የዛጎዌ ስርወ መንግሥት ከ912-1245 አመታቶች ለ330 አመት ያህል የቆዬ ሲሆን 11 ነገሥታት አስተዳድረውታል።እነርሱም መራ ተክለሃይማኖት፣ጠጠውድም፣ጃን ስዩም፣ግርማ ስዩም፣መይራራ፣ሐርቤ 1ኛ፣ይምርሃነ ክርስቶስ፣ቅዱስ ሐርቤ 2ኛ፣ቅዱስ ላሊበላ፣ቅዱስ ነአኩቶለአብ እና ይትባረክ ናቸው።
@በቅዱስ ላሊበላ (1157-1197)እና በቅዱስ ነአኩቶ ለአብ (1197-1237) የኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት:-
24-ጌርሎስ (ቄርሎስ) 1ኛ
25-አባ ዮሐንስ 5ኛ ናቸው።
-አባ ጌርሎስ በአጼ ነአኩቶለአብ ዘመን የነበረ እና ለኢትዮጵያዊው አቡነ ተክለሃይማኖት የድቁና ማዕረግ የሰጠ ነው።አባ ጌርሎስ ከሞቱ በኋላ ግን የግብጽ ሡልጣኖች ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን ጳጳስ ይከለክሉ ስለነበር ከእስክንድርያ ጳጳስ ማስመጣት ስላልተቻለ የኢትዮጵያ ሊቃውንት አቡነ ተክለሃይማኖትን ጳጳስ አድርገው ሾሞዋል።አቡነ ተክለሃይማኖትም በተሰጣቸው ሐይማኖታዊ ሥልጣን በቅንነት ሲያገለግሉ ቆይተው አባ ዮሐንስ 5ኛ ጳጳስነት ተሹመው ከእስክንድርያ ሲመጡ መንበረቸውን ሰጥተው እርሳቸው ወደገደሙት ደብረ ሊባኖስ መኖር ጀምረዋል።
@የዛጉዌ ስርዎ መንግሥት ተጠናቆ የሰሎሞናዊ ስርዎ መንግሥት በአጼ ይኩኑ አምላክ (1253-1268) ከተመሰረተ በኋላ በሁለተኛው ንጉሥ አጼ አግብዓ ጽዮን (1268-1277) የመጡት:-
26-አባ ሚካኤል 4ኛ 27-አባ ስምዖን 3ኛ
28-አባ ጴጥሮስ 3ኛ 29-አባ ማቴዎስ 3ኛ
30-አባ ያዕቆብ 1ኛ ናቸው።አባ ያዕቆብ በአጼ አምደ ጽዮን (1297-1327 አ.ም) የነበሩ ጳጳስ ናቸው።አባ ያዕቆብ የደብረ ሊባኖስ እጨጌ ፊልጶስን ጠርቶ ለሸዋ ኤጲስ ቆጶስ አድርጎ ሹመውታል።
@ከአጼ አምደ ጽዮን በመቀጠል በነገሰው አጼ ሰይፈ አርዕድ (1327-1355) ጀምሮ የነበሩት ጳጳሳት:-
31-አባ ፊቅጦር 1ኛ 32-አባ ቄርሎስ 2ኛ
33-አባ ቆዝሞስ 1ኛ 34-አባ ዮስጦስ 1ኛ
35-አባ ሚካኤል 5ኛ 36-አባ ገብርኤል 4ኛ
37-አባ ሚካኤል 6ኛ 38-አባ ማቴዎስ 4ኛ
39-አባ ዮሳብ 1ኛ 40-አባ ዮሴፍ 1ኛ
41-አባ ቆዝሞስ 2ኛ 42-አባአቃፊላታዎስ
43-አባ ጴጥሮስ 4ኛ 44-አባ ዮሐንስ 6ኛ
45-አባ ፊቅጦር 2ኛ 46-አባ ዮስጦስ 2ኛ
47-አባ በርምያ 48-አባ ሚካኤል 7ኛ
49-አባ ገብርኤል 5ኛ 50-አባ ሚናስ 3ኛ
51-አባ ዮሐንስ 7ኛ 52-አባ ዮሐንስ 8ኛ
53-አባ አብርሃም 2ኛ 54-አባ ማርቆስ 3ኛ
55-አባ መቃርስ 1ኛ 56-አባ ሚካኤል 8ኛ
57-አባ ማቴዎስ 4ኛ 58-አባ ሚካኤል9ኛ
59-አባ ገብርኤል 6ኛ 60-አባ ዮሐንስ 9ኛ
61-አባ ቄርሎስ 2ኛ 62-አባ ሚናስ 3ኛ
63-አባ ማቴዎስ 5ኛ 64-አባሚካኤል10ኛ
65-አባ ገብርኤል 7ኛ 66-አባ ማርቆስ 6ኛ
67-አባ ገብርኤል 8ኛ 68-አባ ማቴዎስ 6ኛ
69-አባ ዮሐንስ 10ኛ 70-አባ ሚናስ 4ኛ
71-አባ ማርቆስ 7ኛ 72-አባክርስቶዶሉ 1ኛ
73-አባ ዘካርያስ 74-አባ ፊላታዎስ2ኛ
75-አባ ሱንትዮስ 76-አባ ገብርኤል9ኛ
77-አባ ዮሐንስ11ኛ
@በአጼ ዘርዓያዕቆብ (1426-1460) የነበሩት:-
78-አባ ሚካኤል11ኛ
79-አባ ገብርኤል10ኛ ናቸው።
@ከአጼ ዘርዓያዕቆብ በመጠል በነገሱት በአጼ በእደ ማርያም (1460-1470) የነበሩት:-
80.በርቶሎሜዎስ
81-አባ ማቴዎስ 7ኛ
82-አባ ዮሐንስ 12ኛ
@በአጼ ናኦድ ዘመነ መንግሥት (1487-1500) የነበሩት:-
83-አባ ማርቆስ 7ኛ
84-አባ ይስሐቅ 2ኛ
85-አባ ከላድያኑ
86-አባ ጴጥሮስ5ኛ
@በአጼ ልብነድንግል ዘመነመንግሥት (1500-1532) የነበሩት:-
87-አባ ማቴዎስ 8ኛ
88-አባ ስምዖን 4ኛ
@በአጼ ገላውዴዎስ ዘመነ መንግሥት(1532-1551) የነበሩት:-
89-አባ ዮሳብ 2ኛ
90.አባሚካኤል12ኛ
91-አባ ማቴዎስ 9ኛ
92-አባ ማርቆስ 8ኛ
@የጎንደር አብያተ መንግሥታት በአጼ ሠርፀድንግል (1555-1589) አ.ም ነው የጀመረው።መንበረ ስልጣኑን ከአጼ ሠርጸድንግል ጀምሮ እስከ ተክለጊዮርጊስ (1773-1771) 18 ነገሥታቶች አስተዳድረውታል።
በእነዚህ ነገሥታቶችም ከእስክንድርያ ጳጳስ እየሾመ ወደ ኢትዮጵያ የተላከ ሲሆን በአጼ ያዕቆብ (1589-1594) እና በአጼ ዘድንግል (1594-1596) ከነበሩት መካከል:-
93-አባ ጴጥሮስ 6ኛ ናቸው።
አቡነ ጴጥሮስ በአጼ ያዕቆብና በአጼ ሱስኒዮስ ጦርነት በወታደር የተገደሉ አባት ናቸው።
@በአጼ ሱስኒዮስ (1596-1624) የነበሩት:-
94-አባ ስምዖን 5ኛ ይባላሉ።አባ ስምዖን 5ኛም አጼ ሱስኒዮስ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖታቸውን በመቀየራቸው አውግዘው ከሎሌው ዮልዮስ ጦርነት ጎን በመሰለፍ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት እራሱን አሳልፎ የሰጠ አባት ነው።በጦርነቱም በጦር ተወግቶ ሞቷል።
@በአጼ ፋሲል (1624-1659) የነበሩት:-
95-አባ ማርቆስ 9ኛ እና
96-አባ ሚካኤል 12ኛ ናቸው። በመሀል የአጼ ፋሲል ወንድም ገላውዴዎስ ያስመጣው
97-አባ ዮሐንስ 13ኛ ይባላል።
@በደጉ አጼ ዮሐንስ 1ኛ (1659-1674) የነበሩት:-
98-አባ ክርስቶዶሉ 2ኛ
99-አባ ሲኖዳ ናቸው።
@በአጼ ኢያሱ አድያም ሰገድ 1ኛ (1674-1698) የነበሩት:-
100-አባ ማርቆስ 10ኛ ናቸው።
@በአጼ ዳዊት 3ኛ (1708-1713) የነበሩት:-
101-አባ ክርስቶዶሉ 3ኛ ይባላል።
@ከዚህ ቀጥሎ በዘመነ መሳፍንት የመጡ ናቸው።ዘመነ መሳፍንት ከትልቁ ራስ አሊ እስከ ትንሹ ራስ አሊ (1777-1845) ለ68 አመታት የቆየ ስርአት ነው።ለሰባት አመት በነገሰው አጼ ሕዝቅያስ የነበሩት:-
102- አባ ዮሐንስ 14ኛ
103-አባ ዮሳብ 3ኛ
104-አባ መቃርዮስ (ጎንደር ሳይደርሱ መንገድ ላይ ሞተው የቀሩ)ናቸው።
105-አባ ቄርሎስ 4ኛ-ኢትዮጵያ በመሳፍንቶች በተከፋፈለች ጊዜ የመጡ ናቸው።
@በአጼ ቴዎድሮስ 2ኛ (1847-1860) የነበሩት;-
106-አባ ሰላማ 3ኛ
107-አባ አትናቴዎስ ናቸው።
@በአጼ ዮሐንስ 4ኛ (1864-1881) የነበረው:-
108-አባ ጴጥሮስ 7ኛ ናቸው።
@በአጼ ምኒልክ ሁለተኛ (1882-1906) እና በንግሥት ዘውዲቱ የነበሩት የኢትዮጵያ ጳጳስ
109- አቡነ ማቴዎስ 7ኛ ናቸው።
ከላይ በዘረዘርነው መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ለ1600 አመታት በግብጽ ኮፒትክ ቤተክርስቲያን ሥር ሁና የራሷን ጳጳስ ሳትሾሞ ዘልቃለች ማለት ነው።ከ1928 አ.ም በኋላ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተከርስቲያን 4 ሊቃውንቶች ወደ ግብጽ ሄደው ሥልጣነ ጵጵስና አግኝተዋል።እነርሱም:-
1-አቡነ ጴጥሮስ
2-አቡነ ሚካኤል
3-አቡነ ይስሐቅ
4-አቡነ አብርሃም ናቸው።
አቡነ ጴጥሮስ እና አቡነ ሚካኤል በፋሽት ጣሊያን በግፍ የተገደሉ የሐይማኖት አርበኞች ናቸው።በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ ፓትርያርክ የነበሩት
110-አቡነ ቄርሎስ ነበሩ።
ጣሊያን ሀገሪቱን በወረራት ጊዜ ፈርተው ወደሀገራቸው ሸሽተው ነበር።በእሳቸው ፈንታ አቡነ አብርሃም ማእረገ ክህነት ሰጥተው ስለነበር ፋሽት ወራሪው ሀገር ለቆ ሲወጣ ተመልሰው በአቡነ አብርሃም እጅ ክህነት የተቀበሉትን ዲያቆናትና ቀሣውስትን እንዳይቀድሱ አወገዙ።
በዚህን ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን ሊቃውንት፣ካህናት፣መነኮሳት እና መምህራን እንዲሁም ምእመናን ጉባኤ አዘጋጅተው መክረው ዘክረው ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስን ወደ ሀገራቸው መልሰው የኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ለመሾም እንቅስቃሴ ጀመሩ።አጼ ሀይለስላሴም የሀሴባቸው ደጋፊ ሆኑ።
ትግሉ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥር 6 ቀን 1943 አ.ም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሊቀጳጳስ ተብለው ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ካይሮ ላይ በግብጹ አቡነ ዮሳብ ሁለተኛ ተሰየሙ።የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንም ከ1951 አ.ም ከሊቀ ጵጵስና ወደ ፓትርያርክነት መንበር ከፍ አለች።ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ሆኑ።
በመቀጠል:-
2ኛ-አቡነቴዎፍሎስ
3ኛ-አቡነ ተክለሃይማኖት
4ኛ-ብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስ
5ኛ-አቡነ ጳውሎስ
6ኛ- አሁን ላይ አቡነ ማትያስ በመንበረ ጵጵስናው ላይ ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!

60 thoughts on “Patriarchs and Blessed Archbishops of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church! P2

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *