The psychology of the masses always matters

ሞራሉ በቀላሉ የማይሰበር ሕዝብ ስነልቦናው ከፍ ያለ ነው!

ሐገር በየትኛውም ጊዜ የእርስበርስ እልቂትና የጦርነት አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል፡፡ አደጋው በራሷ ልጆች አልያም በውጪ ጠላቶቿ ሊከሰት ይችላል፡፡ ስጋት የነበረ፣ ያለና ወደፊትም የሚኖር ነው፡፡

አይደለም በሐገር ደረጃ በግለሰብ ደረጃም ትላልቅ ስጋቶች አሉ፡፡ ማንም ከደቂቃ በኋላ ስላለው ጤናው፣ ሰላሙና ደህንነቱ ማወቅ አይችልም፡፡ አንዳንድ ሁኔታዎች ከምንጠብቀውና ከምንገምተው በላይ ሆነው ከቁጥጥራችን ውጪ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ ስጋትን መተንተን፣ ሊፈጠሩ የሚችሉ ያልታሰቡ ክስተቶችን ማሰብ ነገሮቹ ሲፈጠሩና ከተፈጠሩ በኋላ ለሚኖረው መፍትሄ ወሳኝ ነገሮች ናቸው፡፡

በጥሩም ይሁን በመጥፎ በሕይወታችን ላይ የሚፈጠሩ አዳዲስ ክስተቶች ይዘውት የሚመጡት መልካም አጋጣሚዎችና አደጋዎች መኖራቸው አያጠያይቅም፡፡ የሚሊየን ዶላሮች ሎተሪ የደረሰው ሰው የአዕምሮ ዝግጁነት ከሌለው ዕድሉ አይሆኑ የሕይወት ፈተና ውስጥ ሊሰነቅረው ይችላል፡፡

መከራ አንድም በደስታ ጊዜ፤ አንድም በሃዘን ጊዜ ሊፈጠር ይችላል፡፡ ይሄን ክስተት የሚቀበል የአዕምሮ ዕውቀትና የስሜት ብስለት ከሌለ ወድቆ መቅረትን ያመጣል፡፡ ሐገር ችግሮቿን ተሻግራ፤ መከራዎቿን አልፋ ጸንታ ልትቆም የምትችለው የሕዝቧ ስነልቦና ጠንካራ ሲሆን ነው፡፡ የህዝብ ስነልቦናው መነሻው የግለሰብ ስነልቦና ነው፡፡

በስሜት ብስለት (Emotional intelligence) ያልሰለጠነ ዜጋ ራሱንም ሆነ ሐገሩን ከሚመጣበት መከራ ሊያድን አይችልም፡፡ አስደንጋጭ ክስተት ሲፈጠር አሁናዊ አደጋውንና የሚቀጥለው መዘዙን በእንዴት ያለ መፍትሄ ማስቀረት እንደሚቻል የአዕምሮ ዝግጁነት ከሌለ ከጠፋው በላይ ሌላ ጥፋት ይከተላል፡፡

እንግሊዛውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዋዜማ ላይ ስጋት ወጥሯቸው፣ ፍርሃት ወርሯቸው ጭንቀት በጭንቀት ሆነው እንደነበር ታሪክ ይናገራል፡፡

በዚህ አስፈሪ ጊዜ አዶልፍ ሂትለር በእንግሊዛውያን ላይ የቦንብ ናዳ ለመልቀቅ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ መድረሱ የለንደንን ነዋሪዎች አንቅልፍ ነስቶ ነበር፡፡ ትንሹም ትልቁም ካሁን አሁን የቦንብ ናዳ ረገፈብን በሚል በፍርሃት ቆፈን ተይዞ የለንደንን ሰማይ በየደቂቃው በሰቀቀን ይመለከት ነበር፡፡

በፈረንጆቹ ጥቅምት 19 ቀን 1939 ዓ.ም. ሂትለር ለጦር ጄኔራሎቹ በለንደን ሰማይ ላይ እንዴት ጥቃት እንደሚፈጽሙ እቅዱን አብራራ፡፡ እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 1940 ዓ.ም. ሶስት መቶ አርባ ስምንት የጀርመን ቦንብ ጣይ አይሮፕላኖች ለንደን ሰማይ ላይ ተራወጡ፡፡ ያ ቀን ለእንግሊዛውያኑ ጥቁር ቀን (Black Satureday) ነበር፡፡ በዚህ ቀን የተጀመረው ጥቃት ለተከታታይ ዘጠኝ ወራት ቀጠለ፡፡

በዚህም ከ80 ሺ በላይ የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች በጥቃቱ ሕይወታቸውን አጡ፡፡ በሚሊየን የሚቆጠሩ የለንደን ታሪካዊ ህንጻዎች ፈራረሱ፡፡ ለንደን እንዳልነበረች ሆነች፡፡

ከሁሉ የሚገርመው ይሄን አደጋ እንዴት ነበር እንግሊዛውያኑ ተቀብለው ያስተናገዱት የሚለው ነበር፡፡ እንግሊዛውያኑ ያ ሁሉ ጥቃት ሲፈፀምባቸው ትራፊኩ ስራውን ከመስራት አልታቀበም፤ ህጻናቱ በሰላሙ ጊዜ የሚጫወቱትን ጨዋታቸውን አላቋረጡም፣ ሰራተኛው ከስራው ገበታው አልተስተጓጎለም፡፡

ባለሱቆቹ ከምንጊዜውም በላይ ሱቃቸው በር ላይ ‹‹መስኮቶቻችን በጥቃቱ ቢደቅቁም መንፈሳችን ግን አልደቀቀም፡፡ ደንበኞቻችን ይግቡና የሚፈልጉትን ይሸምቱ! (Our windows are gone. But our spirits are excellent. Come in and try them)›› የሚል ማስታወቂያ ለጥፈው ደንበኞቻቸውን ይጠባበቁ ነበር፡፡

ሂትለር በጊዜው የእንግሊዝን የደህንነት መረጃና የጦር ሚስጥር ቢያውቅም የእንግሊዛውያኑን የመንፈስ ጥንካሬ ግን አያውቅም ነበር፡፡ ዊኒስተል ቸርችል በዚህ ጥቃት ከሶስት እስከ አራት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎቹ ጦርነቱን በመሸሽ ሐገራቸውን ለቀው ይሰደዳሉ ብሎ ቢገምትም የሆነው ግን በተቃራኒው ነበር፡፡

እንግሊዛውያኑ በጥቃቱ ዘመዶቻቸውን በማጣታቸው ሐዘን ቢሰማቸውም፤ ንብረታቸው በመውደሙ ቢበሳጩም ስሜታቸውን የሚያስጨንቅ፣ አዕምሯቸውን የሚረብሽ ምንም ዓይነት የመንፈስ ጠባሳ (Trauma) አልነበረባቸውም፡፡

እንደውም በሰላሙ ጊዜ የነበሩ ወንጀሎች በዚህ ክፉ ጊዜ ቀንሰው ነበር፡፡ የአልኮል ጠጪዎች ከሸመታ ቤት ጠፍተዋል፡፡ ደሃም ይሁን ሃብታም እርስበራሳቸው ይረዳዱ ነበር፡፡ የተጎዱ ቤተሰቦችን በመርዳትና በመጎብኘት ያፅናኑ ነበር፡፡

ፖለቲካ ከሞራላቸው አላነጣባቸውም፤ የካድሬ ጩኸት እርስበራሳቸው አልለያያቸውም፡፡ ይሄ ክፉ ጊዜ ሰው-ነታቸውን አስታወሰ እንጂ ሰብዓዊነታቸውን አልቀማቸውም፡፡ ባንክ ለመዝረፍ የሮጠ የለም፡፡

እስር ቤቶችን ሰብሬ በህግ ጥላ ስር ያሉ እስረኞችን አስለቅቃለሁ ያለ ጉልበተኛ የለም፡፡ ይሄን የቀውጢ ሰዓት ተጠቅሞ ሱቆችን ሰባብሮ እቃዎችን ለመስረቅ ያሰበ ማንም አልነበረም፡፡ በጦርነቱ ምክንያት ኢኮኖሚያቸው እንዳይጎዳ ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠውም ቢሆን ስራቸውን ከመስራት ያቆማቸው አንዳች ሃይል አልነበረም፡፡

ሊንድማን የተባለ የቸርችል የቅርብ ጓደኛ በጦርነቱ ሳቢያ በጣም በተጎዱ በበርሚንግሃምና ኸል (Bermingham and Hull cities) በተባሉ ሁለት ከተሞች እንግሊዛውያኑ የመንፈስ ስብራትና የአዕምሮ መረበሽ እንደደረሰባቸውና እንዳልደረሰባቸው ለማወቅ ሁለት የጥናት ቡድኖችን ወደከተሞቹ ላከ፡፡ አጥኒዎቹም ይዘዉት የመጡት የጥናት ግኝቶች (Findings) ግን ብዙዎችን ያስደነቀ ነበር፡፡ በጥናቱ ወረቀት የፊት ገፅ ላይ በትላልቅ ፊደላት የተፃፈው ፡-

‹‹There is no evidence of breakdown of morale (የሞራል ስብራት እንዳለ የሚያረጋግጥ ምንም ማስረጃ የለም)‹‹ የሚል ነበር፡፡

አዎ ሐገርን ከአደጋ በኋላ ቀና የሚያደርገው ገንዘብ ብቻ አይደለም፡፡ ሐገርን ወደፊት እንዲቀጥል የሚያደርገው የህዝቡ ፅናትና የስነልቦና ጥንካሬ ነው፡፡ እንግሊዛውያኑ የሂትለርንና የቸርችልን ፖለቲካዊ እሰጣ ግባ ችላ ብለው ለሐገራቸው የቆሙት መንፈሳቸው ጠንካራ ስለነበረ ነው፡፡

የመጣባቸውን ጥፋት ተጋፍጠው ሞራላቸውን ሳያስነኩ ሀገራቸውንም ራሳቸውንም ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ አስረክበዋል፡፡ ሞቱን ተቀብለው፤ አካል ጉዳቱን ችለው ሐገራቸው ኢኮኖሚዋ እንዳይወድቅ የበኩላቸውን ሚና ተጫውተዋል፡፡ በዚህም ለሌላው የዓለም ህዝብ ምሳሌ ሆነው ሲዘከሩ ይኖራሉ፡፡

ሐገርን በፅኑ መሰረት ላይ የሚያቆመው ጠንካራ ስነልቦና ያለው ህዝብ ነው! መንፈሱ ከፍ ያለ ሕዝብ ሐገሩ ላይ የተደቀነውን ፈተና ያልፋል፤ ከፊቱ የተጋረጠውን አደጋ ይሻገራል!

አዎ! አጥፊዎች ሆይ… ‹‹ንብረቶቻችንን ልታወድሙ ትችላላችሁ፤ መንፈሳችንን ግን ማድቀቅ አትችሉም፡፡ አካላችንን ትጎዱት ይሆናል ስነልቦናችንን ለመድፈር ግን አቅም የላችሁም!››

ቸር ጊዜ!

ኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ለዘላለም ይኑሩ!

እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)

The morale of the people is not easily broken, the mentality is high!
(The psychology of the masses always matters)

A country can face the danger of genocide and war at any time. The danger may be caused by her own children or by her external enemies. It is a threat that has been, is and will be in the future.

No, there are bigger concerns at the national level and at the individual level. No one can know about his health, peace and safety after a minute. Some circumstances may be beyond our control. Analyzing risk, thinking about potential unforeseen events, and dealing with them after they happen are critical.

There is no question that there are good opportunities and dangers that come with new events in our lives, whether good or bad. If the person who wins the million dollar lottery is not mentally prepared, chances are that life’s challenges will fail him.

Suffering and happy times; One can also develop during times of grief. If there is no mental knowledge and emotional maturity to accept this event, it will lead to failure. The country has overcome its problems. She can overcome her hardships and stand firm only when her people’s psyche is strong. The origin of public psychology is individual psychology.

A citizen who is not trained in emotional intelligence cannot save himself or his country from suffering. When an alarming event occurs, if there is no mental preparation on how to avoid the immediate danger and the subsequent consequences, other disasters will follow.

History tells us that the British on the eve of World War II were worried, scared and anxious.

During this terrible time, Adolf Hitler made the final decision to drop the bomb on the British, and the Londoners were left awake. Both the little and the big ones were watching the London sky with awe every minute, in fear that now the sound of the bomb had hit us.

On October 19, 1939 Hitler explained his plan to his generals on how to attack the London skyline. In the year September 7, 1940 Three hundred and forty-eight German bombers flew over London. That day was Black Saturday for the British. The attack that began on this day continued for nine consecutive months.

As a result, more than 80,000 innocent citizens lost their lives in the attack. Millions of London’s historic buildings were destroyed. It was as if London had never been.

The most surprising thing was how the British accepted and handled this disaster. When the British were attacked, the traffic did not refrain from doing its work. The children did not stop playing in peacetime, the worker was not interrupted from his work table.

The shopkeepers wrote on the door of their shop, “Even though our windows were broken by the attack, our spirit was not broken.” Our customers come in and shop what you want! (Our windows are gone. But our spirits are excellent. Come in and try them)” and they were waiting for their customers.

Although Hitler knew British security information and military secrets at the time, he did not know the strength of the British spirit. Winstle Churchill predicted that about three to four million of his citizens would flee their country because of this attack, but the opposite happened.

Although the British were saddened by the loss of their relatives in the attack; Although they were upset by the destruction of their property, they did not have any kind of trauma to disturb their feelings or disturb their minds.

In fact, the crimes that existed during the peace were reduced during this evil time. Alcoholics are gone from shopping malls. Whether they were rich or poor, they helped each other. They comforted the bereaved families by helping and visiting them.

Politics did not make them moral. The shouts of the cadre did not separate them from each other. This bad time reminded them of their humanity, not their humanity. No one ran to rob a bank.

I will break the prisons and release the prisoners under the shadow of the law, there is no bully. No one thought to use this time of crisis to smash shops and steal goods. There was no force that stopped them from doing their work, even if they put themselves in danger so that their economy would not be damaged because of the war.

Lindman, a close friend of Churchill, sent two research groups to the cities of Birmingham and Hull, which were badly affected by the war, to find out whether the British suffered mental breakdowns or not. But the research findings that came with the bones surprised many. Written in large letters on the front page of the research paper:-

There is no evidence of breakdown of morale.

Yes, money is not the only thing that keeps a country upright after a disaster. It is the perseverance and psychological strength of the people that keeps the country moving forward. The British ignored the political threats of Hitler and Churchill and stood up for their country because their spirit was strong.

Faced with the disaster that came to them, they preserved their country and themselves without losing their morale and handed it over to the next generation. Accept his death. They have played their part in preventing their country’s economy from collapsing. In this way, they will be remembered as an example to the rest of the world.

It is a strong minded people that will put a country on a solid foundation! A nation whose spirit is high will pass the test that has been imposed on the country. He will overcome the danger that is in front of him!

Yes! Destroyers… “You can destroy our properties; But you cannot crush our spirit. You may harm our bodies, but you have no power to dare our minds!

Good time!

Long live Ethiopia and the spirit of Ethiopianism!

May the smell be blessed (E.B.Y.)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *