the wind and the sun an Aesop’s fable

ፀሐይ እና ነፋስ

ፀሐይና ነፋስ ረጅም መንገድ አብረው ጉዞ ጀመሩ፡፡
እነዚህ ጓደኛሞች አብረው እየሔዱ ጨዋታ አንስተው ሲያወሩ ነፋስ ፀሐይን አንድ ጥያቄ ጠየቃት «ሰዎች የምትፈልጊውን ነገር እንዲያደርጉልሽ የምታደርጊያቸው በምንድን ነው?» ሲል ነፋስ ጠየቃት ።

ፀሐይም የነፋስን ጥያቄ ሰማችና «እኔማ ከሰዎች የምፈልገውን መጠየቅ ብፈልግ በጣም ቢቆጡ፣ ቢሳደቡ እንኳን ቀስ አድርጌ በትህትና በፍቅር ረጋ ብዬ እጠብቃቸውና የምፈልገውን እንዲሰጡኝ /እንዲያደርጉልኝ/ አደርጋለሁ» አለችው፡፡

ነፋስ ወዲያውኑ ቀበል አደረገና «በጣም ተሳሳትሽ የምን መለማመጥ? የምትፈልጊውን ለማግኘት በጉልበት መጠቀም ነው እንጂ» አለ፡፡
ፀሐይ እንደሱማ አይቻልም» አለች፡፡

ነፋስም እኔ እችላለሁ ተመልከች «ያ» መንገድ ላይ የሚጓዘውን ሰውዬ በደቂቃ ውስጥ ልብሱን በየተራ ብትንትን አድርጌ አስወልቀዋለሁ» ሲል ፎከረ፡፡

ነፋስም በአንዴ ኃይሉን አነሣና የሰውየውን ልብስ ለማስወለቅ መታገል ጀመረ፡፡ ይኼኔ ሰውየው ልብሱን እንዳይወስድበት በኃይል ልብሱን ጭብጥ አድርጎ አስጣለ /አዳነ/፡፡

ነፋስም ሰውየው ስላሸነፈው ተናደደና አዋራ አስነሥቶ ሰውየው ዐይን ላይ በትኖበት ጥሎት ሔደ፡፡ ፀሐይም በመገረም እየተመለተችው

እሺ አያ ንፋስ አሸንፈህ የፈለከውን አገኘህ)» ብላ ጠየቀችው ነፋስም «ይገርምሻል ልብሱን አልለቅም ሲለኝ አዋራ አንሥቼ ዐይኑ ላይ ጨመርኩበት» አላት፡፡

  ፀሐይ ሳቅ እያለች «አይ አያ ነፋስ፡፡ በትግል አልሆን ሲልህ በጉልበት ለመጠቀም ሞከርክ? ግን እንደዚህ አይደለም እኔን አስተውለህ ተመልከተኝ» አለችውና ልታሳየው ወደ ሰውየው ሔደች፡፡

  ሰፊ ከሆነው ከሰማይ መቀመጫዋ ብድግ አለችና ሰውየውን ገና ጠዋት ከሚመጣው ሙቀቷ ሰላምታ አቀረበችለት ሰውየውም የፀሐይን ሙሉ ፈገግታና ትህትና በጣም ደስ አሰኝቶት ከሙቀቷ ስር ቁጭ አለ፡፡ 

እንደገና ከሰዓት በኋላ መንገድ ሲሔድ ሰላም አለችውና ከሙቀቱ ጭምር አደረገች፡፡
«በጣም ስለሞቀህ ለምን ኮትህን አታወልቅም?» ስትል ጠየቀችው ደስ ብሎት ምንም ሳይከፋው ፈጠን ብሎ «እሺ» አለና ውልቅ አድርጎ ያዘው፣ አሁንም ሙቀቷን ጨመረችና

«ሸሚዙን ብታወልቀው» አለችው አወለቀው ሙቀቷ በጣም እየጨመረ መጣ፡፡
«ለምን በቀዝቃዛ ውኃ አትታጠብም ስትል ቀስ አድርጋ ጠየቀችው በጣም ደስ ይለኛል አለና ሰውነቱን በቀዝቃዛ ውኃ አስነከረችው፡፡»

ይሔኔ ነፋስ በጣም ደነቀው፡፡ በራሱ ኃይለኝነት በጣም አፈረ፡፡ ሰዎች ነፋስን ብርድ በመጣ ቁጥር የበለጠ እየፈሩት ወደ ሙቀት እንደሚሸሹት አወቀ፡፡

ሐይ ግን በትህትና በፍቅር ሰዎችን ስለምትቀርብ ወደ ቅዝቃዜ ብትወስዳቸው እንኳን ቅር አይላቸውም፡፡ በደስታ እንደሚከተሏት ተመለከተ፡፡ የፀሐይን ጥሩ ፀባይ በጣም አደነቀ፡፡

ልጆች ከሰፈር አብሮ አደጎቻችሁ ከትምህርት ቤት ጓደኞቻችሁ እንዲሁም ከወላጆቻችሁ ጋር አብራችሁ ስትኖሩ የምትፈልጉትን ለማግኘት በመሳደብ፣ በኃይል፣ በመማታት አይደለም፡፡

ነፋስን አይታችኋል አይደል? ክፉና ኃይለኛ መሆን ሰዎች እንዲርቁን እንዲጠሉን አዋቂዎችም እንዲረግሙን ያደርገናል፡፡

እና ልጆች ልክ እንደ ፀሐይ ጥሩና ደግ ትሁትና ታዛዥ ሆናችሁ ሰዎትን ብትቀርቡ ሁሉም ይወዳችኋል፣ ይመርቃችኋል፡፡
❤️መልካም ሰንበት ❤️

Sun and wind

The sun and the wind started a long journey together.
When these friends were walking and talking together, the wind asked the sun a question, “How do you make people do what you want?” Wind asked her.

The sun heard the wind’s question and said, “If I want to ask people what I want, even if they get angry, even if they insult me, I will wait for them gently and lovingly and make them give me what I want.”

The wind immediately accepted and said, “You are very wrong, what are you trying to do?” “It’s about using energy to get what you want,” he said.
She said, “It is not possible for the sun to rise.”

“Look, I can handle the wind. In a minute, I can take off the clothes of that person walking on the road,” he boasted.

The wind suddenly raised its strength and began to struggle to remove the man’s clothes. So that the man did not take his clothes from him, he forcibly threw off his clothes.

The wind got angry because the man had defeated him and picked up an aura and threw it at the man’s eyes. The sun followed him in surprise

Okay, Aya, did you win the wind and get what you wanted?” she asked him. And the wind said, “It’s strange, when he told me not to let go of his clothes, I picked up the awara and added it to his eyes.”

   The sun laughed and said, "No wind." Did you try to use force when he told you not to fight? But it's not like that, notice me and look at me." She went to the man to show him.

   She jumped up from her wide seat in the sky and greeted the man from her early morning warmth, and the man sat down under her warmth, much to the full smile and humility of the sun.

Again in the afternoon she said hello to him as he was walking, even from the heat.
“You’re so hot, why don’t you take off your coat?” She asked him, he was happy, he quickly said “OK” without any offense and held him outside, she still increased her heat.

“If you take off his shirt,” she said, he took it off, and her heat was rising.
“Why don’t you take a bath in cold water?” she asked him slowly.

He was very surprised by the wind. He was very ashamed of his own power. He found that the colder the wind, the more people fear it and run away to the warmth.

But because you approach people with humility and love, they don’t mind even if you take them to the cold. He saw that they were happily following her. He greatly admired the good nature of the sun.

When children live together with your neighbors, schoolmates, and parents, you don’t have to abuse, force, or fight to get what you want.

You’ve seen the wind, haven’t you? Being mean and powerful makes people shun us, hate us, and adults curse us.

And children, if you approach your people as good, kind, humble and obedient as the sun, everyone will love you and praise you.
❤️ Happy Sabbath ❤️

10 thoughts on “the wind and the sun an Aesop’s fable

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *