Whoever hates his brother is a murderer…

ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው…(1ኛ ዮሐ.3፡15)

“ብሔርተኛ የሆነ አምባገነናዊ አገዛዝ ለጊዜው ምክንያታዊነት በጎደለው ስሜታዊና ግልብ በሆነ አስተሳሰብ ዜጋውን ወይም “ብሔር” ብሎ ከፋፍሎ ያደራጃቸውን በመንዳት የተሳካለት ይምሰለው እንጂ፣ አገዛዙን ለማስቀጠል ሲል የሚፈጽማቸውን ግፎች በሂደት ሕዝቡ እየተገነዘበው ስለሚሄድ ምንም ዓይነት ሴራ ቢጠቀም አገዛዙ ያሰበው እቅድ ዘለቄታ ሊኖረው አይችልም፡፡

በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃን ይሁን አናሳ ቁጥር ባለው “በብሔር” ማንነት
ላይ የተመሠረተ ማንኛውም አገዛዝ የሳይንሳዊ ፖለቲካዊ ስርአት ሳይሆን በአዕምሮ ቅዠት ህመም የተጠቃ፣ ፋሽስታዊ አምባገነን፣ ኢ-ሰብአዊ፣ ስርአተ አልበኛ፣ የወሮበላና የደንቆሮ ገዢ ቡድን ነው፡፡ በአጠቃላይ “የብሔርተኛ ፋሽስታዊ አገዛዝ በፖለቲካ ሳይንስ የተቃኘ ሕዝባዊ አስተዳደር ሳይሆን፣ ከአዕምሮ ቅዠት ህመም የመነጨ የድንቁርና አገዛዝ ነው::

በአሁኑ ዓለም የመልካም አስተዳደር ሳይንሳዊ ፖለቲካ ማለት፣ የአንድ ሀገርን ብዙሃን ሕዝብ አዕምሮ ከፖለቲካዊ ቁጭት፣ ጥላቻና በቀል ነጻ በማድረግ በኑሮ ደረጃዉ እያሳደገ የማስቀጠል ብቃት ነው፡፡

በአንድ ሀገር መንግሥታዊ አገዛዝ ላይ ብዙሃኑ ሕዝብ አዕምሮ ውስጥ ቁጭት፣ ጥላቻና በቀል ከተፈጠረ ሀገሪቱ የብዙሃን ሕዝብ ድጋፍ የተቸረው የአገዛዝ ሥርዓት ባለመሆኑ ሀገሪቱ ያልተረጋጋችና ልማቷም ዘለቄታ የሌለዉ ስለመሆኑ ማሳያ ነው፡፡

ይህም ቁጭት፣ ንዴትና ጥላቻ እያደገ በመሄድ በዋናነት በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያን የመሳሰሉትን ሀገራት ሁልጊዜ ወደ እርስ በርስ ጦርነት እየከተተ ዜጋውን ወደተሻለ ኑሮ እንዳያድግ የሚገድብ ነው፡፡

ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው…(ኛዮሐ.3፡15)፡፡ አንድ ሰው ግድያ ከመፈጸሙ በፊት የሚፈጠረው የጥላቻ አስተሳሰብ ይቀድማል፡፡ የጥላቻውም አስተሳሰብ በሂደት በግድያ ድርጊት ይፈጸማል፡፡

በአንድ ሀገር ውስጥ ብዙሃኑ ሕዝብ በፊት ስለሚገድለው ሰው በአዕምሮው ውስጥ ቁጭት፣ ንዴትና ጥላቻን የሚፈጥር መንግሥት ካለ አምባገነን አገዛዝ እንጂ፣ መንግሥታዊ ስርአት አይደለም፡፡

ስርአት ማለት ማንም ሰው እንደፈለገው የማይቀያይረው፣ በሳይንሳዊ እውቀት የተደራጀ፣ ህግንና ደንብን በመከተል የታለመለትን ግብ የያዘ ተቋም ነው፡፡

“የብሔርተኛ” አምባገነናዊ አገዛዝ ሳይንሳዊ የፖለቲካ ስርአት ሳይሆን፣ በባህሪው በቀሪው ዜጋ አዕምሮ ውስጥ ሁልጊዜ ቁጭት፣ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ንዴትና ጥላቻን የሚፈጥር የስርአተ አልበኛና የአሸባሪነት አገዛዝ ነው፡፡

የብዙሃኑ ህዘብ አዕምሮ ለቁጨት፣ ለንዴትና ለጥላቻ የሚዳርግ አገዛዝ ይዋል ይደር እንጂ፣ አንድ ቀን በብዙሃኑ ህዝብ አመጽ በውርደት መወገዱ እንደማይቀር የአሁኑ ዓለም ታሪካዊ ሃቅ ነው፡፡

በአሁኑ ዓለም “በብሔር” ማንነት ላይ የተመሠረተ ፋሽስታዊ አገዛዝ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚዊ እንዲሁም በኃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ እንኳ ሳይቀር የበላይነቱን በማረጋገጥ ሰውን ከሰው የሚለይ፣ የሚያገልና አድልኦን የሚፈጽም ሳይንሳዊ ያልሆነ አገዛዝ ነው፡፡

ስለሆነም በብዙሃኑ ሕዝብ ዘንድ ምንጊዜም ቢሆን ተቀባይነት ስለሌለው ሁልጊዜ ሰላምና መረጋጋትን በማሳጣት ለአብዮት የሚዳርግ ነው፡፡

በ”ብሔር” ማንንነት አዕምሮ በተቃኘ ፋሺስታዊ አገዛዝ ውስጥ ሁሉም ባይቀበለውም ነገር ግን እጅግ አብዛኛው ዜጋ በ”ብሔር” ማንንነት አዕምሮ ቅዠት ህመም ይለከፋል፡፡

የ”ብሔርተኛ” ፋሽስታዊ አገዛዝ የስልጣኑን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ሲል የሚያራምዳቸው መሠረታዊ ሴራዎች አሉት፡፡

እነዚህ ሴራዎችም በህዝብ አዕምሮ ውስጥ ቁጭት፣ ንዴትንና ጥላቻን በአገዛዙ ላይ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመሩ ይሄዳሉ፡፡

በመሆኑም ይህ ቁጭት፣ ጥላቻ ይዋል ይደር እንጂ “በብሔር” ማንነት ተከፋፍሎ የነበረውን ሕዝብ ወደ መተባበበር ይገፋፋውና አገዛዙን ለማስወገድ የሞት ሽረት ትግል ውስጥ ሳይወድ በግዱ ይገባል፡፡

ሰብስቤ አለምነህ

Whoever hates his brother is a murderer… (1 John 3:15)

“A nationalist dictatorial regime seems to be successful by dividing the citizenry or “nation” and organizing them with an irrational, emotional and lopsided thinking for the time being, but the people are gradually realizing the pressures they will carry out in order to maintain the regime, so the regime’s plan cannot be sustained if it uses any kind of conspiracy.

Whether it is a majority or a minority in a country, the “national” identity
Any regime based on it is not a scientific political system, but a delusional, fascist dictator, inhumane, anarchic, thug and deaf ruling group. In general, “Nationalist Fascist regime is not a public administration studied by political science, but a regime of ignorance born from the disease of mental illusion.”

In today’s world, the scientific politics of good governance is the ability to free the minds of the masses of the people of a country from political resentment, hatred and revenge and continue to raise their standard of living.

If there is resentment, hatred and revenge in the minds of the majority of the people of a country, it is a sign that the country is unstable and its development is not sustainable because the government is not supported by the majority of the people.

This is growing frustration, anger and hatred, mainly in Africa, which is always pushing countries like Ethiopia into civil war and restricting the citizens from developing a better life.

Anyone who hates his brother is a murderer… (John 3:15). A hateful attitude precedes a person’s murder. The attitude of hatred is gradually carried out in the act of murder.

If there is a government in a country that creates resentment, anger and hatred in the minds of the majority of the people about the person they kill in front of them, it is a dictatorship, not a governmental system.

A system is an institution that cannot be changed by anyone, is organized by scientific knowledge, and follows the rules and regulations that have the intended goal.

A “nationalist” totalitarian regime is not a scientific political system, it is an anarchist and terrorist regime that always creates frustration, anxiety, fear, anger and hatred in the minds of the rest of the citizens.

It is a historical fact of the present world that sooner or later, a regime that causes anger, anger and hatred in the mind of the majority of the people, will be removed in disgrace one day by the rebellion of the majority of the people.

In today’s world, a fascist regime based on the identity of a “nation” is an unscientific regime that separates, discriminates and discriminates people from each other by asserting its supremacy in social, political, economic and even religious matters.

Therefore, because it is not always accepted by the majority of people, it always leads to revolution by depriving peace and stability.

Although not everyone will accept it in a fascist regime that is obsessed with the identity of the nation, the vast majority of citizens suffer from the illusion of the identity of the nation.

The “nationalist” fascist regime has basic conspiracies to ensure the continuation of its power.

These conspiracies are increasing frustration, anger and hatred towards the regime in the public mind.

Therefore, sooner or later, this resentment and hatred will push the people who were divided by “national” identity to unite and reluctantly enter into the fight to the death to remove the regime.

You are the world

9 thoughts on “Whoever hates his brother is a murderer…

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *