Thinking or speaking? Which is better value?

ማሰብ ወይስ መናገር? የቱ የተሻለ ዋጋ አለው?

ለማዳ እና አጫዋች ወፍ ለመግዛት ወደ ሱቅ የሄደ ሰው አንዲት የምትናገር ወፍ ለመግዛት ዋጋ ቢጠይቅ በጣም አስወደዱበት። “እንዴት ይህችን የምታህል ትንሽ ወፍ በዚህ ብር ትሸጣለች?” ብሎ ተገረመ። ከዚያ ወደ ቤቱ ተመልሶ ያቺ ሚጢጢ ወፍ ይህን ያህል ካወጣች ይሄንማ ብሸጠው ሀብታም ያደርገኛል” ሲል በጥራጥሬ ያፋፋውን ዶሮ ታቅፎ ወደዚያ ሱቅ በፍጥነት ሄደ። ከዚያም ለባለ ሱቁ እያሳየ “ይሄን ዶሮ ውሰደው ልሽጥልህ?” አለው። ባለሰቁም “ዋጋው ስንት ነው” አለው።

ባለ ዶሮውም ፈርጠም ብሎ የበቀቀኗን ሁለት እጥፍ ብር ጠራበት። ይህን ጊዜ ባለሱቁ በጣም እየተበሳጨ “ጤነኛ አይደለህም እንዴ? እንዴት እንዲህ ትላለህ? በቀቀኗ እኮ በመጠን ብታንስም ስለምትናገር ነው የተወደደችው። አንተ ምን ልትል ነው?” ቢለው ባለ ዶሮው “አዎ ልክ ነው ያንተ ትናገራለች። የእኔ ግን ፈላስፋ ነች ታስባለች” አለው።

ማሰብ ወይስ መናገር? የቱ የተሻለ ዋጋ አለው?

ሰው ላይ ከተጣሉ ተፈጥሮአዊ ኃላፊነቶች ውስጥ አንዱ ማሰብ ነው። በአካል ትንሽ እና ደካማ የሆነውን ሰው ከግዙፋኑ እንስሳት በላይ የሚያሰለጥነውና ገዢያቸውም የሚያደርገው ይህ የለባዊነት (ምክንያተኝነት) ጸጋው ነው። ይሁን እንጂ ብዙ ሰው ይህን ውድ ጸጋ የሚጠበቅበትን ያህል ሲጠቀምበት አናይም። አንድ ጸሐፊ በቀልድ መልክ “ከምናገኛቸው ሰዎች ጥቂቶቹ የሚያስቡ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ስለማሰብ የሚያስቡ፣ የቀሩት ብዙዎች ደግሞ ከማሰብ ይልቅ ሞታቸውን የሚመርጡ ናቸው” ይላል።

በእርግጥም “እኔ እንደማስበው” ብሎ ንግግሩን መጀመር የሚችለው ልዩው ፍጡር ሰው በንግግሩ ውስጥ የሚታየው ትልቁ ክፍተት ግን “አለማሰቡ” ነው። ሐሳብ ትልቅ ኃይል አለው። በጎነትም ሆነ ክፋት የሚጀምረው ከማሰብ ነው።

በሐሳብ ካልበደልህ በሥራ በደለኛ ልትሆን አትችልም። የሲዖልን በር አይተኸዋል? የገነትስ ደጅ የት እንደ ሆነ ጠይቀህ ታውቃለህ? መልሱን እኔ ልንገርህ፤ ሁለቱም ደጆች ያሉት ልብህ ላይ ነው።

አስበህ በተናገርከው ቃል፣ ተናግረህ በፈጸምከው ተግባር ወይ የገነትን ወይም የሲዖልን በር ትከፍታለህ። ሰው የተሰጠውን ትልቅ የማሰብ ጸጋ አለመጠቀሙ ብቻ ሳይሆን መጠቀም ሲጀምር ደግሞ የሚያስባቸው ክፉ ነገሮች የበለጠ ያሳዝናሉ።

እንደውም አንዳንዶች “ጥሩ ካላሰብህ ብዙ አታስብ” የሚሉት ለዚህ ይመስላል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን “ብዙ አታስብ” ከሚለው ምክር የሚበልጥ ሌላ መፍትሔ አለው። ይኸውም ልብን ለእግዚአብሔር መስጠት።(ምሳ 23፥26) ልባችን የመልካሙ አምላክ ማደሪያ ከሆነ ከእርሱ የሚወጣው ሐሳብ ሁሉ መልካም እና የተቀደሰ ይሆናል። ያን ጊዜ ጠቢቡ እንደ ተናገረው አፋችን የሕይወት ምንጭ ከንፈሮቻችንም ደስ የሚያሰኝ ነገር ሁሉ የሚፈልቅባቸው ይሆናሉ። ዲያቆን አቤል ካሳሁን

If a person who went to the store to buy a pet and a toy bird asked for a price to buy a talking bird, they would love it. “How can a small bird of this size be sold for this much money?” he wondered. Then he went back to his house and said, “If that little bird spends this much, if I sell it, it will make me rich.” He hugged the chicken that he had puffed up with grain and hurried to that shop. He called the parrot two times the money. This time, the shopkeeper was very upset, “Are you not healthy? How do you say that? Although the parrot is small in size, it is loved because it talks. What are you going to say?” The chicken said, “Yes, you are right. “But she thinks she’s a philosopher.”

Thinking or speaking? Which is better value?

One of the natural responsibilities of man is to think. It is this rationality (rationality) that trains the physically small and weak man above the giant animals and makes them their ruler. However, we do not see many people using this precious grace as much as they should. A writer jokingly says, “Of the people we meet, some think, some think about thinking, and the rest many would rather die than think.” Indeed, the special being who can start the conversation with “I think”, but the biggest gap in the conversation is “not thinking”.

Thought has great power. Both good and evil begin with thought. If you are not guilty in thought, you cannot be guilty in action. Have you seen the gates of hell? Have you ever wondered where the gates of heaven are? Let me tell you the answer. Your heart has both doors. With the words you think and speak, with the actions you speak and perform, you either open the door of heaven or hell.

Not only does he not use the great gift of thinking that has been given to man, but when he starts to use it, the evil things he thinks are even more deplorable. In fact, that’s why some say, “If you don’t think well, don’t think too much.” But the Bible has a better solution than the advice to “don’t think too much.” That is, giving the heart to God. (Proverbs 23:26) If our heart is the abode of the good God, every thought that comes out of it will be good and holy. Then, as the sage said, our mouth will be the source of life and our lips will be the source of all pleasant things.

Deacon Abel Kasahun

13 thoughts on “Thinking or speaking? Which is better value?

  1. Hi, just required you to know I he added your site to my Google bookmarks due to your layout. But seriously, I believe your internet site has 1 in the freshest theme I??ve came across.Seo Paketi Skype: By_uMuT@KRaLBenim.Com -_- live:by_umut

  2. Hi, just required you to know I he added your site to my Google bookmarks due to your layout. But seriously, I believe your internet site has 1 in the freshest theme I??ve came across.Seo Paketi Skype: By_uMuT@KRaLBenim.Com -_- live:by_umut

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *