Easter fasting weeks – 4
መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም አራተኛ ሳምንት)ቅዱስ ያሬድ የዐቢይ ጾምን በሰየመበት አጽዋማት ላይ አራተኛው ሳምንት መፃጉዕ በመባል ይታወቃል፡፡መፃጉዕ ማለት ትርጓሜው በቁሙ ሲፈታ “ጐባጣ” ማለት እንደሆነ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ላይ ፈትተውታል፡፡መፃጉዕ የስያሜው ዋና ታሪክ፥በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ በምትባልና አምስትም መመላለሻ በነበረባት አንዲት መጠመቂያ ሥፍራ ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ…